ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ።
13 ሚያዝያ 2018
ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሻሻለ የፋይናንስ አስተዳደር ይበልጥ ለማዘመን፣ ተጠያቂነትንና የአሰራር ግልፀኝን ለማጐልበት በተዘጋጀዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
2ኛ. በከተማዉ እየተገነባ ያለዉን ሰፊ የቤት ልማት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረዉ፣ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሪፎርም በማጠናከር እና የማስፈፀም ብቃት ለማሳደግ በተዘጋጀዉን ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
3ኛ. የመሬት ማስፋፍያ ለጠየቁ ተኪ ምርት ለሚያመርቱ ኢዱስትሪዎች፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል የፈጠሩ ፕሮጀክቶች፣ ሆቴሎች እንዲሁም፥ በከተማ አስተዳደሩ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የሚያስችል መሬት በምደባ ለማስተላለፍ የቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ፣ ተፈፃሚ እንዲሆን አድፅድቋል።