ዜና
ሀገር ለጠቢባን የሕያው ሥራዎቻቸው ምስክር ሐውልት ታቆማለች!
27 ሚያዝያ 2018
ዛሬ በአርበኞች ቀን በተለያዩ መስኮች የጀግንነት ሚና የተወጡ አርበኞቻችንን በማስታወስ እየዘከርናቸው ነው።
ሀገር በልማት ስራዎች፣ ድንበርን በመከላከል፣ በሰንደቅ ዓላማ እና በሕግ ብቻ አትገነባም። ሀገር የምትገነባው በሕዝብ የጋራ ትውስታ፣ በጋራ ስሜት እና በታላላቅ የጥበብ ውጤቶችም ጭምር ነው። ይህ እውነት ዛሬ በቆሙት የሀገር ባለውለታ ታላላቅ ጠቢባን ሐውልቶች በአዲስ አበባ ከተማችን እውን አድርገናል።
ከተማ አስተዳደራችን በኮሪደር ልማት እና በታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ ጥበብን ማዕከል አድርጓል።
ዛሬ ሃውልት የቆመላቸው ለሃገራቸው ሰላም፣ ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለነፃነትና እኩልነት ላቀነቀኑት አንጋፋዎቹ የሀገር ባለውለታዎች ሎሬት ጸጋዬ ጸጋዬ ጋብረ መድኅን፣ የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ ዓሊ ቢራ፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር እና ሐጫሉ ሑንዴሣ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪም ልናከብራቸው የሚገባን የሀገር ባለውለታዎች የሆኑ የጥበብ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ይህ ስራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም።
ጥበብ ሀገርን ትስራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች።
ፍጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ