የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራን የሚከታተል የድጋፋዊ ክትትል ቡድን በቢሮ ምልከታ አካሄደ
08 ሚያዝያ 2018
በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ በመጀመሪያው ዙር (Wave 1) ወደ ዝግጅት ምእራፍ የገቡ የከተማ አስተዳደር ቢሮዎችን የስራ እንቅስቃሴ ለመገምገምና ለመደገፍ የሚያስችል ከክልል እና ከፌደራል ሚኒስቴር መስሪያቤት የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን በቢሮው ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የመንግስት አስተዳደር አገልግሎት ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ በቢሮው የበላይ አስተባበሪነት ወደ ሪፎርሙ የገቡ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህም ሀገራዊ ሪፎርሙን ወጥነት ባለው መልኩ ለመምራት እንዲቻል ከፌደራል እስከ ክልል እና ወረዳዎች ድረስ እንዲተገበር ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስራ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በእለቱ በክትትልና ድጋፉ ላይ ተገኝተው መልክታቸውን ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር እንደተናገሩት የሀገራዊ ሪፎርሙ መሳካት ተቋማት አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመዱ ለማስቻል እና የሚታዩ ክፍተቶችን በድጋፍ ለመሙላትና መልካም ተሞክሮዎችን ለመቀመር ክትትልና ድጋፉ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱ በበኩላቸው በሪፎርም ትግበራ ወደ ተቀራረበ ደረጃ ለማምጣትና ለማናበብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቢሮው የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡