Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ሐሙስ, 08 ሚያዝያ 2018 4:33 ከሰዓት
Last updated
April 16, 2026 16:33
Weather
addis ababa 🌦 +22°C
ዜና

" በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! "

08 ሚያዝያ 2018

" በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! "
" በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! " " በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! " " በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! " " በቂ አቅርቦት ከሸማች እስከ አምራች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ !! "

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የ2018 የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለቀናት የሚቆይ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፍቷል።

ባዛሩም የንግድ፣ የስራና ክህሎት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም የአርሶአደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ ነው።

ባዛሮች አምራቾችን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት የገበያ ትስስር በመፍጠር ገበያን የሚያረጋጉ፣ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ዕድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን ተገልጻል፡፡

ባዛሩን በይፋ የከፈቱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንደገለፁት በተለያዩ ወቅቶች የሚከፈቱት ባዛሮች አምራቾችን ከሸማቾች ጋር ቀጥታ በማገናኘት አምራቹን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡

ምርቶችን ከአርሶ አደሩ ቀጥታ ወደ ገበያ በማቅረብ በዓልን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ገልፀዋል።

እነዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ገበያን በማረጋጋት የኑሮ ውድነት ጫናውን የማቅለልና በበዓላት ወቅት ህብረተሰቡ ምርቶችን በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የጎላ ሚና እንዳላቸውም  ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የኑሮ ውድነትን በመቀነስና ገበያ በማረጋጋት ረገድ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም  ገበያ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በቀናት በሚቆየው የባዛር ዝግጅት ላይም ለበዓል የሚያስፈልጉ ሁሉም ምርቶች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ግብይታቸውን እንዲፈፅሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ በዓሉ ዋዜማ እንዲሚቆይ ተገልጿል።