ዜና
እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች የድል በአል አደረሳችሁ!
27 ሚያዝያ 2018
የአርበኞች ቀንን በደማቅ ሁኔታ ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አፅቀስላሴ ፥የባህር ሃይል ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ፥ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን እና ጀግኖች አርበኞች በተገኙበት ልዩ ሆኖ በኮሪደር ልማት በተዋበው የአራት ኪሎ ፕላዛ ላይ አክብረናል።
አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሕይወታቸውን ሳይሳሱ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት፣ ዛሬ በነጻ ሕዝቦች ፊት በኩራት የምትጠራዋን ሉዓላዊት ሀገራችንን ኢትዮጵያን አቆይተውልናል።
ይህንን ዘመን ተሻጋሪ እውነት እና ምትክ የማይገኝለት የታሪክ መስዋዕትነት ትውልድ ፈጽሞ አይዘነጋውም።
የዛሬው ዘመን ትውልድ የአባቶቹን መታወሻ እና የታሪክ ቅርስ ከመዘከርና ከመጠበቅ ባሻገር ሌላ አዲስ የአርበኝነት እውድ ሊፈጥር ይገባዋል።
የትላንቱ አርበኝነት ሀገርን ከባዕድ ወራሪ ማዳን እንደነበር ኹሉ፣ የዛሬው አርበኝነት ደግሞ ሀገርን ከድህነት፣ ከኋላቀርነት እና ከተመጽዋችነት ማላቀቅ ነው።
ጀግኖች አባቶቻችን ወራሪውንም ሆነ የውስጥ ባንዳውን ታግለው አሸንፈው ሀገር እንዳቆዩልን ኹሉ፣ እኛም ዛሬ የልማት እና የሰላም ጉዟችንን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትን የዘመኑን ባንዳዎች በአንድነት፣ በንቃት እና በሥራ ማሸነፍ ግድ ይለናል።
በድጋሚ እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች ቀን አደረሳችሁ።
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኑር !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ