Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ረቡዕ, 03 ሰኔ 2018 12:10 ጥዋት
Last updated
June 10, 2026 00:10
Weather
Addis Ababa: ☀️ +17°C
ዜና

በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር!

07 ግንቦት 2018

በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር!
በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር! በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር! በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር! በበጎነት መንደር፤ ተጨማሪ የበጎነት ተግባር!
 
ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት አንዱ የተስፋ ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን፣ ዛሬ በልደታ ክፍለ-ከተማ ለክፍለ-ከተማው 3ኛ የሆነ 29 ኛውን የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል።
በገነባነው 492 ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ 2,460 ለሚሆኑ ነዋሪዎቻችን እፎይታ በሆነው በተለይም በርካታ አረጋውያን፣ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን እንዲሁም ለልማት ተነሺዎች በሚኖሩበት የበጎነት መንደር ውስጥ ድጋፍ ለሚገባቸው ወገኖች ዛሬ ምገባ ያስጀመርንበት የምገባ ማዕከል ተጨማሪ የበጎነት ስራ ነው ።
ንፁህ፥ ትኩስ ምግብ በቀን አንድ ጊዜ የሚቀርብባቸው በሁሉም ክፍለ ከተማ 29 የምገባ ማዕከላት ውስጥ መመገብ ስለሚቻል፤ ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችን ምግብ ፍለጋ ወደ ጎዳና የሚያስወጣ ምክንያት በከተማችን ስለሌለ፤ በማዕከላቱ በመገኘት መመገብ ትችላላችሁ። በዚህ የበጎነት መንደር የስራ እድል የተፈጠረባቸው የእንጀራ መጋገሪያ ማዕከል፣ የልብስ ስፌት፣ የፀጉር ስራና የልጆች መጫወቻ ለነዋሪዎቹ ሌላኛው የእፎይታ ምንጭ ናቸው።
ሁሌም ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ያለው ዳሽን ባንክ ጥሪአችንን ተቀብሎ ለማዕከሉ ግንባታ እና በቀጣይም ለመመገብ ላደርገልን ድጋፍ በራሴና በተጠቃሚዎች ስም ክልብ እመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ