ለተጠባባቂ አመልካቾች ጥሪ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ ለአዲስ መሶብ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት መ/ቤት በተለያዩ የስራ መደቦች ለማወዳደር በ28/06/2018 ዓ.ም ፈተና መፈተኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት፣ በተጠባባቂነት ስማችሁ የተመዘገበ አመልካቾች ከነገ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ማስረጃችሁን (ኦርጂናል እና ኮፒ) እንዲሁም ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ፣ አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የአዲስ መሶብ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ዋናው መ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
የተጠባባቂዎችን ስም ዝርዝር ለመመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡ https://www.aacapsjobs.gov.et/