Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ረቡዕ, 07 ሚያዝያ 2018 11:40 ከሰዓት
Last updated
April 15, 2026 23:40
Weather
addis ababa 🌦 +17°C
ዜና

የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

07 ሚያዝያ 2018

የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!
የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!! የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!! የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!! የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

ዛሬ በታሪካዊቷ ቀን በመጋቢት 24 ዕለት ለከተማችን  በጉለሌ ክፍለ ከተማ 6ተኛውንአዲስ መሶብ ዲጂታል  አንድ ማእከልየመንግሥት አገልግሎትን  ስራ አስጀምረናል

መጋቢት 24 ኢትዮዽያን ወደ አዲስ ምዕራፍ የማሻገር  ቃል ኪዳን የተገባበት ታሪካዊ ቀን ነው። አገራዊ ለውጡ የመጣው ለሁሉም፣ ከሁሉምና በሁሉም ነው። ከለውጡ ወዲህ የሚታዩና ተጨባጭ የሆኑ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡት በጋራ ጥረታችን ነው። ይህ ለውጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ስብራቶቻችን እንዲጠገኑና ወደ ከፍታ እንድንጓዝ እጅግ ጠንካራ መሰረት የጣለ  ነው።

እንሰራለን፤ እንችላለን!” ብለን በጋራ በተነሳንባቸው ዓመታት፣ ከኋላ ቀር የፖለቲካ ባህሎች ተላቀን  ችግሮችን በውይይትና በምክክር የመፍታት ሂደት ላይ ገብተናል። ስምንት ዓመታት፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር ወደ ዘመናዊ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ  ለመገንባት  በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገብን እንገኛለን።

የተሰበሩ ማህበራዊ እሴቶችን በማከም ማህበራዊ ፍትህ እንዲነግስ የሚስችሉ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም  በከተማችን የሚገኙ በሚሊዮኖች  የሚቆጠሩ ወገኖችን በተለይም የሀገር ባለውለታዎችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች ከአስቸጋሪ ኑሮ አውጥተን የሰውን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲኖሩ አድርገናል።

ባዶ ምሳ ዕቃ ይዘው ወደ ትምህርት ገበታ ይመጡ የነበሩ ሕፃናትን እኩል በልተውና  ለብሰው  እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ፣ አዲስ አበባን ሕፃናትን ለማሳደግ  ተመራጭ ከተማ አድርገናታል።

ሌላው ስኬት የመንግስት የተቋማት ስብራትን በመጠገን  ነፃ፣ ገለልተኛ የአገልጋይነት መንፈስን የተላበሰ ጠንካራ  ተቋማት የመገንባት ሽግግር ነው።

ለዘመናት  የአገልግሎት ዘርፉን ለመለወጥ  ሳይቻል ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትቦ የኖረ ቢሆንም የለውጡ መንግስት ቃል በገባው መሰረት ችግሩን ሥር ነቀል በሆነ መልኩ የሚለውጥ 'የመሶብ' ዲጂታል አንድ ማዕከልን በመተግበር ለተገልጋዩ እፎይታን ይዞ መጥቷል።

 የነዚህ  የለወጥ ፍሬዎች ዋንኛ ተጠቃሚ የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብም ማልዶ ወደ አደባባዮች በመውጣት የዘወትር ድጋፋን እንደገና አጽንቷል።

ጅማሬያችን ትላንት ቢሆንም ከህዝባችን ጋር ያሳካነው ድል እና የደረስንበት ርቀት ቀላል አይደለም።

የኢትዮዸያን ብልፅግና ሊያስቀረው የሚችል አንዳችም ምድራዊ ሀይል የለም!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ