Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ማክሰኞ, 12 ጥር 2018 6:11 ጥዋት
Last updated
January 20, 2026 06:11
Weather
Addis Ababa weather unavailable
ዜና

የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ገመገመ

30 ታኅሣሥ 2018

የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ገመገመ

የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ገመገመ

 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ የማናጅመንት አባላት በተገኙበት መድረክ ግምገማ አካሄደ።
​በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የግምገማ መድረኩ አስፈላጊነት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በመፈተሽ፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ በጋራ ለመቅረፍ መሆኑን ተናግረዋል። አፈጻጸሙን መገምገም ተቋማዊ አቅምን ለማደበርና በቀሪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መሠረት እንደሚሆንም ኃላፊው ገልጸዋል።
​በመድረኩ የቢሮው የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ደፋር፤ በስድስት ወራቱ በቢሮው ሥር ባሉ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።
ሪፖርቱን ተከትሎም ከተሳታፊዎች ሰፊ አስተያየቶችና ግብዓቶች የተነሱ ሲሆን፣ የቀረበው የሥራ አፈጻጸም ይበልጥ በሚዳብርበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
​ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበርና የቢሮው የሥራ አመራሮች ከቢሮው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በሪፖርቱ ላይ መካተትና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።
​በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ የየዘርፉ ኃላፊዎችና አጠቃላይ የማናጅመንት አባላት ተገኝተዋል። በመጨረሻም በቀሪው የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ የታቀዱ ተግባራትን በላቀ ጥራትና ፍጥነት ለማከናወን የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።