Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ማክሰኞ, 13 ሚያዝያ 2018 7:03 ከሰዓት
Last updated
April 21, 2026 19:03
Weather
addis ababa: ☀️ +24°C
ዜና

ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ

12 ሚያዝያ 2018

ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ
ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጦችን በተሞክሮ በመቀመር ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ

ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማገዝ ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በማስቻል እረገድ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ከተከናወኑት ተግባራት ውስጥ ለሌሎች ተቋማት በተሞክሮነት ለማስፋት የሚያስችሉ ሲስተሞችን የመለየትና የማስፋት ስራ ይከናወናል፡፡

በተለይም ከተገልጋዩ ማህበረሰብ የአገልግሎት ፍላጎት ጋር ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸውን ተግባራት በመለየት በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማምጣት አዳዲስ እና የተሻሻሉ የአገልገሎት ሲስተሞችን በማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

በዚህም መሰረት በየካ /ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት አልምቶ ወደ ተግባር ያስገባቸው የአገልግሎት ስታንዳርድ ምዝገባ ሲስተም (customer service system) እና /ቤቱ ከየካ ጽዳት አስተዳደር /ቤት ጋር በመተባበር ያለማውን በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዘመናዊ ስርዓት ዝርጋታ ላይ በዳታ ቤዝ አድምኒስተሬተር እየለማ ያለ ቴክኖሎጂ ወደ ስራ በማስገባት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የየካ /ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት ኃላፊ አቶ ኪያ ቱኩ ለተሞክሮ በቀረብት ሲስተሞችል ግምገማ በተደረገበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

የአገልግሎት ስታንዳርድ ምዝገባ ሲስተም በዋናነት አገልግሎት ሰጪው ለአገልግሎት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት ለማህበረሰብ እንዲሰጥ በማድረግ ተገልጋይ ተኮር ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል መሆኑን የገለፁት የጽ/ቤት ኃላፊው አገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ሁኔታ በቅርበት ለመከታተል ጭምር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በፅዳት አስተዳደር /ቤት በኩል የበለፀገው በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዘመናዊ ስርዓት ዝርጋታ ላይ በዳታ ቤዝ አድምኒስተሬተር ሲስተም በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ስርአት ላይ ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያግዝ እንዲሁም የክፍያ ስርአቱን በማዘመን የደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ የሚሰሩ ማህበራትን ከጽ/ቤቱ ጋር ከወረቀት ነፃ በሆነ አሰራር በማስተሳሰር አገልግሎቱን ለመከታተል እንደሚረዳ ተመልክቷል።

በቀረቡት የአገልግሎት መስጫ ሲስተሞች ላይ አስተያየት የሰጡት በቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት አመራርና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት /ከተማው በራስ ተነሳሽነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለማዘመን ከፅ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት ያለማቸው ሲስተሞች ችግር ፈቺና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ እሴት የሚጨምሩ መሆናቸውን ገልፀው ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል።

በቀጣይም በተሰጡት ሀሳቦች ላይ ማስተተካከያ በማድረግ የምርጥ ተሞክሮውን ለሌሎች የማስፋት ስራ እንደሚከናወን ተመልክቷል።