ቢሮው የረመዳን ፆምን ምክኒያት በማድረግ የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ፡፡

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መጋቢት 13 ቀን 2016ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የረመዳን ፆምን ምክኒያት በማድረግ ከክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ሀላፊዎችና የቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች ጋር በጋራ በመሆን የኢፍጣር ስነስርዓት አካሂዷል፡፡

በኢፍጣር ስነ-ስርዓቱ ላይ መልክታቸውን ያስተላለፉት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እንደተናገሩት ሀገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም ሀይማኖት ተከታዮች ተቻችሎ የመኖር ተምሳሌት እንደመሆኗ መጠን የጋራ ሀገር እንዳለችን በማሰብ በጋራ በመተሳሰብ መንፈስ በአንድነት ለመስራት በመቆም አብሮነታችንን ማስመስከር ይገባናል ያሉ ሲሆን ለእምነቱ ተከታዮች መልካም የረመዳን ወር ይሁንላችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡