ቢሮ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ዛሬም ለሶስተኛ ዙር ቀጥሎ ተካሂዷል፡

ፐብሊክ ሰርቨስ ቢሮ፤ መጋቢት 16 ቀን 2016ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከስራ ሰአት መግቢያ በፊት ሰኞ ማለዳ በሚያዘጋጀው የሰራተኞች የጋር መዓድ መቋደስና የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሩና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፐብሊክ ሰረቪስና የሰው ሀብ ልማት ቢሮ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደገለፁት ከተቋም ግንባታ በፊት ሰዎች የግል መለያቸውን ወይም የገፅታ ግንባታ በማድረክ በስራ ከባቢ፣ በማህበራዊ ኑሮ ተስማሚነታቸውን ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የሰዎች መለያ (personal branding) የሚመነጨው ከባህሪ፣ከብቃት፣ከተስጦው፣ከማንነትና ከተግባር አንፃር የመነሳ በመሆኑ ሰዎች የራሳቸውን መለያ ለመገንባት ከነዚህ በመነሳት ውጤታማ መለያቸውን መገንባት ይቻላቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡