በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ
Addis Ababa Public Service & Human Resource Development Bureau

  • Sine Up Now
  • መነሻ
  • ስለእኛ
    • የቢሮ ሃላፊ መልዕክት
    • የተቋሙ ታሪክ
    • ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች
    • ስልጣንና ተግባር
    • ተቋማዊ መዋቅር
    • ሃላፊዎችና ዳይሬክተሮች
    • አግኙን
  • ዜና እና ሚዲያ
    • ትኩስ ዜናዎች
    • ፎቶዎች
    • ቪዲዎች
  • አገልግሎቶች
    • የአስተዳደር ፍርድ ቤት
    • ቅሬታን የመቀበልና ምላሽ የመስጠት
    • የማማከርና ድጋፍ
    • የሰው ኃብት ስምሪት
    • የስልጠና አገልግሎት
    • የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን
    • የአበልና ጥቅማ ጥቅም ጥናት
    • የመረጃ አገልግሎት
  • ማስታወቂያ
    • ማስታወቂያዎች
    • ክፍት የስራ ቦታ
    • ጨረታዎች
  • መረጃዎች
    • አዋጆች
    • መመሪያዎች
    • ሰነዶች
    • ጥናቶች
  • አግኙን
  1. Home
  2. About Us

Power & Duties

  1. Home
  2. Message

የቢሮው ስልጣንና ተግባር

  • ተቋም አቅም ግንባታ ስራን የሚያሳልጡ ዘመናዊ አሰራሮችንና ተሞክሮዎችን በመለየት በከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ አስፈላጊዉን የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤
  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀብት ልማት በቀጣይነት የሚለማበትንና ጥቅም ላይ የሚዉልበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ይተገብራል ፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤
  • የተቋማት አደረጃጀት ጥናት ላይ አስፈላጊዉን ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤ አግባብነቱን ይመረምራል፣ ያጸድቃል፤
  • የከተማው አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራት ጥናት ያካሂዳል፤ ውጤቱን ለካቢኔ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተገቢዉን ይፈጽማል፤
  • በከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተገቢዉ ስታንዳርድ መኖሩን ያረጋግጣል፤ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤ ያጸድቃል፤ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤
  • በከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻፀም ይከታተላል፣ የተገልጋዩን እርካታ ጥናት ያካሂዳል፣ የጥናቱን ውጤት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
  • የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለዉ መንገድ መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን እንዲሁም ዉጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
  • ያልተማከለ የአስተዳደር ስርዓትን ለማጠናከር የሚያስችል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
  • የመንግስት ሰራተኞችን ወቅታዊ አፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፤
  • የመንግስት ሰራተኛ በብቃትና በአፈጻፀም ላይ የተመሰረተ የምደባ፣ የደረጃ ዕድገትና የእርከን ጭማሪ፣ የጥቅማጥቅምና የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ዉጤታማነቱን ይገመግማል፣ አስፈላጊዉን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፤
  • አግባብ ያላው የፌደራል ሕግ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመንግስት ሰራተኛዉ የሚያስፈልጉ የስራ መደቦች፣ የትምህርት የስልጠናና የስራ ልምድ አጠቃላይ መመዘኛዎች ያወጣል፤
  • የመንግስት ሰራተኞች አቀጣጠር፣ አመዳደብ፣ የደረጃ እድገት፣ ዝዉዉር፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም፣ ስልጠናና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፤ በህግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
  • በህግ መሰረት የከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ለማቆየት በሚቀርብ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፤
  • የከተማ አስተዳደሩን የሰዉ ሀብት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ያደራጃል፤
  • የህዝብ አገልጋይነት አስተሳሰብ ያለዉ አመራርና ፈጻሚ ይገነባል እንዲገነባ ይሰራል፣ የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤ ያረጋግጣል፤
  • በሚዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮች፤ አደረጃጀቶችና ማኑዋሎች ዙሪያ አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  • ሁሉም ተቋማት ዉጤታማ አፈጻፀም እንዲኖራቸዉ የሚያደርጋቸዉን አዳዲስ የለውጥ መሳሪያዎች ከራሳቸዉ ባህርይ አንጻር አጥንተው እንዲያቀርቡ ያበረታታል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፡፡
  • ስለእኛ

    የተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዕሴቶችና ስትራቴጂካዊ የትኩረት መስኮች

    Read More
    ክቡራን ተገልጋዮቻችን ማገልገል ክብር ነው! እኛም እናንተን ዝቅ ብለን ስናገለግል ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማና... Read More

    ለፈጣን መረጃ

    • መግቢያ
    • ስለእኛ
    • ዜናዎች
    • ማስታወቂያ
    • አግኙን

    በዚህ ያግኙን

    • አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 6
    • 4ኪሎ ቅደስተ ማሪያም ቤተክርስትያን አልፎ
    • ስፖርት ኮሚሽን ህንፃ ከ8ኛ አስከ 12ኛ ፎቅ
    • ስልክ: +251-11-849-4092
    • ኢሜል: addisababa@pshrdb.gov.et

    © 2023 PSHRDB. All Rights Reserved

    Social Midea Developed By: Demis Az