ቢሮው ከተቋማት ሪፎርሙን ለሚከታተሉ ለሚደግፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለክፍለ ከተሞች እና የክፍለ ከተሞች ፐ/ሰ/ጽ/ቤት የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ምዘና ቡድን መሪዎች የተግባራት የእስታንዳርድ እና ንፅፅር ስልጠና መስጠት ጀመረ።

አዲስ አበባ መስከረም 10/12016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከተቋማት ሪፎርም ለሚከታተሉና ለሚደግፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለክፍለ ከተሞች እና የክፍለ ከተሞች ፐ/ሰ/ጽ/ቤት የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ምዘና ቡድን መሪዎች የተግባራት እስታንዳርድና ንጽጽር እና የእለት ከእለት እቅድ ክንውን መመዝገቢያና ማነጻጸርያ ቅጾች ትኩረት በማድረግ ስልጠናው መሰጠት ጀምሯል።

በዕለቱም የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬትና የሪፎርም ቡድን መሪ አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና አላማ ሰልጣኞች በወሰዱት ስልጠና ላይ መነሻ በማድረግ በተቋማቸው በአቻ ፎርም ስለ ተግባራት እስታንዳርድ እና ንጽጽር ያገኙትን የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰረት በማድረግ በተቋማቸው ስልጠናውን እንዲያጋሩና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል ።

የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ብርሃኑ እንደተናገሩት

ስለ ተግባራትና ንጽጽር የወረደላቸውን ተግባራት መሰረት በማድረግ በፊት ከነበረው ተግባራት በተሻለ መልኩ የተገልጋይ እርካታን መፍጠር እንግልት ለመቀነስ ፣ብልሹ አሰራርን እና ተገልጋይን በእኩል አይን ከማየት አንጻርና ፈጣንና ቀልጣፍ አሰራርን በማከናወን የተግባራት ንጽጽር ጥራትን ፣ ጊዜን ፣መጠን ባገኙት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰረት ሁሉም ተቋማት በተግባራት አሰጣጥ ላይ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በፈጣን ጊዜ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስችል ገልፀዋል።