የስምምነቱ ዝርዝር መረጃዎች
- የመዝገብ ቁጥር
- 0003
- የተፈረመበት
- January 3, 2026
- የሚቆይበት ጊዜ
- January 3, 2026 – January 3, 2017
አጋሮች
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የስምምነቱ ዝርዝር መረጃዎች
አባሪ
ወሰን
የከተማችን አስተዳደር ባለፉት የለውጥ አመታት ያስመዘገባቸው በርካታ ስኬታማ ስራዎች እንዳሉ ሆኖ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሁንም ከማህበረሰቡ የሚነሱ ችግሮች እንዳሉ ይታወቃ፡፡ይሄንንም ለመፍታት ባለፉት አራት አመታት የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል ስኬታማ ውጤት አስመዝግበናል።ከተማችንን ወደ ምርጥ ከተሞች ለመቀየር የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ክፍቶችን በመለየት ሪፎርም የተሰራ ሲሆን አገልግሎቶች/ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ የሚያስችል ተግባራት ተከናውኗል።
ለስማር ሲቲ ግንባታ አጋዠ የሚሆነና ለአስቀመጥነው ፍኖተ ብልጽግና ስኬታማ ጉዞ ማሳያ የሆነ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣት በቅርብ የከፈትነው አዲስ መሶብ አገልግሎት ትልቅ ስኬት ተደርጎ በመወሰድ ይህንኑ ለማስፋት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው።ሰፊ የህዝብ አገልግሎት ያለባቸውን ተቋማት በመለየት አገልግሎቱን ለማዘመን የሚያስችል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያመጧቸው ለውጦች ትልቅ ሲሆን ይህን አጠናክሎ ለማስቀጠል የቅንጅት ስራ ወሳኝ ነው። የሰራተኛው የገቢ አቅምን ለማጠናከርና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ ድጎማዎች፣ ለአገልግሎት እንዲተጋ የሚያደርጉ ትራንስፖርት እንዲሁም በቅርብ የተደረገው የደሞዝ ጭማሬ ትልቅ አቅም ሲሆን ሰራተኛው ጋር ያለውም የአመለካከት የአቅም ክፍት መሰረት በማድረግ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናና የስራ ቦታውን ምቹ በማድረግ የተጀመረው ጥረት የሚበረታታ ነው።ይሄም የአገልጋይነት መንፈስን በማሳደግ የአገልጋዩን እርካታ እያሳደገ የሚገኝ ነው፡፡
በሌላ በኩል ምንም እንኳን ለዘመናት የተከማቹ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል በተለየ ትኩረት የተሰራው የአገልግሎት ውጤታማነት እና አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የተሰሩ ስራዎች ውጤት ሰፊ ቢሆንም አሁንም የተሟላ የማህበረሰብ እርካታ ያልፈጠርንና ሌብናትና ብልሹ አሰራርን በምንፈልገው ደረጃ አለማድረሳችን የሚታወቅ ነው።የተለወጠ፣ ለማገልገል ብቁ እና ውጤታማ አገልጋይ ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ዛሬም ቢሆን ለአገልግሎት አሰጣጡ እንቅፋት የሚሆንና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ለመክበር ሌት ተቀን የሚሰሩ ሰራተኛችን ቁጥሩ ቀላል አይደለ። ለሙያው የሚመጥን የተለያዩ ስልጠናዎች አቅሙን የሚገነባ ባለሙያ እንዳለ ሁሉ የአቅም ክፍተት ያለበትም ሰራተኛ ቁጥሩ ቀላል አይደለም።
አገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ እርካታው እያደገ የመጣ መሆኑ በጥሩ ቢወሰድም መንግስት ለመድረስ ከሚያስበው አንጻር ክፍት እንዳለ የማይካድ ነው። በመሆኑም ይሄን የሚቀይር ስራ በቀጣይ ይሄን መቀየር ይጠበቃል።የአገልግሎትና ቴክኖሎጂ ክላስተር ዋናው ተልኮ የሚሆነው የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የማህበረሰቡን እርካታ ለማሳደግ በመሆኑ ለዚህ የሚሆኑ የተለያዩ ተግባራት በማቀድ መስራትና የፍኖተ ብልጽግናን ጉዞን በመደመር መንግስት እሳቤ መምራት ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል።
ዋና ዋና ዘርፎች
ከአጭር ጊዜ አንጻር
❖ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማነት ማሳደግ፤
❖ የሰራተኛውን አቅም በማሳደግ ለቦታው የሚመጥን ሰራተኛ
መፍጠር/መገንባት፤
❖ የማህበረሰቡን ንቃለ ህሊና በማሳደግ ለአገልግሎት አሰጣጡ የህብረተሰቡን
ድርሻ ማሳደግ፤
❖ ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር የሰራተኛውን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ
አደረጃጀቶች በመፍጠር የኢኮኖሚ ቸግሩን በመፍታት የኑሮ ደረጃው
ማሳደግ፤
❖ የሚሰሩ ስራዎችን በህዝብ ግንኙነት ስራዎች ማጀብ በአገልግሎት አሰጣጡ
ያሉ ሁኔታዎችን ለህብረተሰብ ማሳወቅ፤
4.1.2
ከመካከለኛ ጊዜ አንጻር
❖ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መቀነስ፤
❖ አዳዲስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ማሳደግ፤/
❖ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዪ ክተቶችን በመድፈን የማህበረሰቡን
እርካታ ማሳደግ፤
❖ በአጠቃላይ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ የአደረጃጀት ክፍተቶችን
በመለየትና በማረም ሪፎርሙን በማጠናከር ክፍተትን መሰረት ያደረገ ተቋም
ግንባታ ስራዎች በመስራት ብቃትን መሰረት ያደረገ ሰው ሀብት ስምሪትን
በማረጋገጥ ብዝሃነትና አካታችነትን በማስከበር የአገልጋይነት መንፈስን
በማጠናከር የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድግና ወቅቱን የሚመጥን ዘመናዊ
አገልግሎት በመስጠት ልምድ የሚቀሰምበት ከተማ መገንባት ይሆናል፡፡