
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/1/2016 ቀን2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የስልጠናና የሙያ ብቃት ዳይሬክቶሬት ለ3ኛ ዙር ያዘጋጀው ስልጠና ተጠናቀቀ።
በእለቱም የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት በቢሮ የስልጠናና የሙያ ብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘመናይ ሸገና እንደገለፁት ሰልጣኞች የመግቢያና የመውጫ ፈተና መዉሰዳቸዉ ከስልጠናው መልስ ምን ተልዕኮ ይዘው መሄድ እንዳለባቸውና ያገኙትንም የአቅም ግንባታ ስልጠና ልምድ በመውሰድ ከመደበኛ ስራቸው በተጨማሪ ተቋማቸውን ለመለወጥ የተሻለ እቅድ ለማቀድ እንሚረዳቸው ጠቁመዋል።
ዳይሬክተሯ አክለውም ሰልጣኞች በተቋማቸው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበሩ ችግሮችንና ክፍተቶች በመለየት የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሰሩ ሲሉ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ስልጠናውን አስመልክቶ የእውቅና ሽልማት ሰርተፍኬት ተበርክቷል።