
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 ቀን 2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የስልጠናና የሙያ ብቃት ዳይሬክቶሬት ለተከታታይ 10 ቀናት በሰጠው ስልጠና በእውቀት የታገዘ አሰራርን ለመከተልና የተቋማትን የአሰራር ስርአት ከማዘመን አኳያ በበጀት ዓመቱ በዝግጅት ምዕራፍ ተገቢነት ያላቸው ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ከተቋማት እስከ ክ/ከተማና ወረዳዎች በየደረጃው የተውጣጡ ሰልጣኞች ገልፀዋል፡፡
የምልከታና የክህሎት ችግሮችን ከመቅረፍ አንፃር ከስራ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ስልጠናዎች ተዘጋጅተው መሰጠታቸው አገልግሎት አሰጣጥ ስርአት ላይ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ገልፀው የእቅድ አዘገጃጀት ላይ የሚፈትሽ ስልጠና እንደመሆኑ መጠን ወደ ተሰማሩበት ተቋምና የስራ መስክ ስልጠናውን በማውረድ የተግባር እቅድ በመንደፍ በአዲስ ጉልበትና እውቀት ለመስራት መዘጋገታቸውን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ሰልጣኞች እንደገለፁት ከስልጠናው ጎን ለጎን የስልጠና አካባቢውን ምቹ ከማድረገ አንፃር ለእናት ሰልጣኞች ለልጆቻቸው የህፃናት ማቆያና ምገባን ከመስጠት ባሻገር የህክምና አገልግሎት መሰጠቱ፣ የካፍቴሪያ አገልግሎቱ ሰዓቱንና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በተቀናጀ መንገድ መሰጠቱ ለሌሎችም ተቋማት አርአያ መሆን የሚችል ስራ መሰራቱን ገልፀው ስልጠናው የተዘጋጀበትን ተቋም አመስግነዋል፡፡