ቢሮዉ ከአገልግሎት አሰጣጥ፤ከዝውውርና መሰል ጉዳዮች ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመቅረፍ እና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ክፍት የስራ መደቦችን ለሟሟላት ከነ ባለሙያ ስያሜያቸዉ የልየታ ስራ እያገባደደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፤ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ኃብት ልማት ቢሮ ለ2016 በጀት ዓመት በያዘዉ እቅድ መሰረት የሰራተኛውን መረጃ አያያዝ ግልፅና ተደራሽ ለማድረግ በማቀድ መረጃ የማጥራትና የመተንተን ስራ እያገባደደ እንደሚገኝ በቢሮ የሰው ሀብት ስምሪትና መረጃ አያያዝ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ለገሰ ገልፀዋል፡፡

በየደረጃው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከዝውውርና መሰል ጉዳዮች ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ክፍት መደቦችን ከነባለሙያ ስያሜያቸው በመለየት ስራው ወደ መገባደዱ መድረሱንም ጭምር ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም በበጀት ዓመቱ በዋነኛነት ሶስት ቁልፍ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰራ ገልፀው እነዚህም ፍትሃዊ የሰው ሀብት ስምሪት ስራን ጨምሮ የተቀናጀ የሰራተኛ መረጃ አያያዝ /ኢስሚዝ/ ወረቀት አልባ የመረጃ አያያዝን በመጠቀም አጠቃላይ የሰራተኛውን መረጃ በቴክኖሎጂ የማስደገፍ እስትራቴጂ ከመንደፍ በተጨማሪ በመዝገብ ቤት የመገኙ የነባር ሰራተኞችን ፋይል ወደ ዲጂታል የመረጃ አያያዝ ስርዓት የመስገባት ስራዎች በዋነኝነት መያዛቸውን አብራርተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ አገልግሎት ሰጪው አካል የተቀመጠውን ስታንዳርድ ተከትሎ ከማገልገል ባሻገር የራስ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በመላበስ ራስን ማብቃት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡