ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ጳጉሜ 1 የሚከበረውን የአገልጋይነት ቀን ሰራተኛው ህብረብሄራዊነትንና የመደመር እሳቤን በሚያጎላ መልኩ ህብረተሰቡን በቅንንትና ፈገግታ በተሞላበት ሁኔታ በማገልገል እንዲያከብር የእቅድ ገለጻ እና አቅጣጫ ለተቋማት አመራሮች መስጠቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23 ቀን 2015ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ጳጉሜ 1 የሚከበረውን የአገልጋይነት ቀን ህብረብሄራዊነትንና የመደመር እሳቤን በማጉላት ህብረተሰቡን በቅንነትና በፈገግታ በማገልገል እንዲከበር ኦረንቴሽንና አቅጣጫ ለተቋማት አመራሮች ገለፃና ውይይት አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደተናገሩት አገልጋዩ የአገልጋይነትን ስሜት በማዳበር የህብረተሰቡን እርካታ በማሳደግ የእኩል ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰው በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት መነሻ እቅዱን ወደ ተቋማቸው በማውረድ ቀኑን በአገልግሎት እንዲያሳልፍ ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመድረኩ ላይም የአገልጋይነት ቀን የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተው ለተቋማት የማሳወቅ ስራ የተሰራ ሲሆን ከማዕከል እስከ ወረዳ እንዲሁም ከሴክተር ተቋማት ጋር ወጥነት ባለው መንገድ በመናበብ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ተጠቅሷል፡፡