ከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጡ ቀድሞ ከነበረው 2015 በጀት ዓመት በተጠናከረ መንገድ ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ። ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነሀሴ 22/2015

በከተማ አስተዳደር ደረጃ ጳጉሜ 1የሚዉለዉን የአገልግሎት ቀን ለማክበር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ።

ጳጉሜ 1የሚከበረውን የአገልግሎት ቀን ምክንያት በማድረግ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን አንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ለ2016 በጀት አመት ተገልጋይ ተኮር አገልግሎትን በይበልጥ ለማጠናከር ማቀዱን ተከትሎ ጳጉሜ 1ቀን በሁሉም ተቋማት በተለየ መልኩ አገልግሎት እንደሚሰጥ እና በተለይም በጤና ተቋማትና የትራንስፖርት አገልግሎት በተለየ መልኩ በዕለቱ ግልጋሎት እንደሚሰጡ አስታዉቀዋል። ኃላፊዋ አክለውም በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እለቱን ጨምሮ በበጀት ዓመቱ በቅንነት፣በታማኝነትና እና ትህትናን በተላበሰ መንፈስ አገልግሎት መስጠት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።