ቢሮው የ2016 በጀት አመት የአሰራር ጥናት አስመልክቶ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከሚገኙ ከተመረጡ ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

አዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 22/ 2015

የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማረጋገጥ ተቋማት ቴክኖሎጂ መር አሰራርን መከተል እና ለህዘብ አገልግሎት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን በማዘጋጀት አዳዲስ አሰራሮችን መፍጠር እንዳለባቸው ተገለፀ።

በውይቱም የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን እንደገለፁት ሪፎርም ለማድረግ የተመረጡ ተቋማት ተገልጋይ ይበዛባቸዋል ተብለው የተለዩ መሆናቸውን ገልጸው ሪፎርም ሲደረግ እያንዳንዱ ተቋም ሶስቱን የእይታ መስክ በመከተል ህጎችን በማሻሻል የህዝቡን ስሜት በመረዳት አደረጃጀቱን መቀየር እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ አርአያና ፈር ቀዳጅ በመሆን በሌሎች ተቋማት ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን መንገድ መፍጠር እንዳለባቸውም በውይይቱ አንስተዋል።