
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነሀሴ 18/2015 ዓ.ም
በዕለቱ በመክፈቻው የተገኙት የፐ/ሰ/የሰ/ሃ/ልማ/ቢሮ የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቴሬት አቶ አድሄና ተበጀ ስልጠናውን አስመልክተው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያለዉ የሰዉ ኃይል ለተቋም ግንባታ ከፍተኛ ሚና ያለዉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየደረጃው የሚገኙ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን ለማጎልበት ስልጠና ወሳኝ ሚና እንደሚኖረዉ ገልፀዋል፡፡
ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸዉ በክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ አሰጣጥ /monitoring and evaluation/በአይነታዊ የጥናት አሰጣጥ ዘዴ /qualitative research methloogy/ አና በአገልግሎት አሰጣጥ የአገልግሎት ስታንዳርድ /service delivery and service standard/ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና የሚያገኙ መሆኑን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ከነበራቸው ልምድ በመነሳት በቂ እውቀት ማግኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡