ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክ/ከተማ ዘመናዊ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል አስመርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፤

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃው ላይ እንደተናገሩት፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስንገነባ ለተገልጋዩ መቀመጫና ለአገልግሎት መስጫ ስፍራ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል ታልሞ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ በከተማችን የአስተዳደር ወረዳዎችን ስማርት ስናደርግና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በውስጡ የቴክኖሎጂና ዳታ ቤዝ በመዘርጋት ማህበረሰቡ በዘመኑ ቴክኖሎጂ ዲጂታል አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግና ተደራሽ ተደርጎ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል።

በቀጣይ ሰራተኞችን በዘመናዊ አሰራር ላይ አቅም ግንባታ መስጠት፣ ወረቀት አልባ አሰራርን ማስቀረት፣ ነዋሪዎቻችንን ደግሞ በዲጂታል አገልገሎት እንዲያገኙ ማስተዋወቅና ማለማመድ፣ እገዛ የሚያደርጉ የሰው ሀይልን ማሟላት ላይ እንሰራለን ሲሉም ገልፀዋል።

መሰረታዊ ልማቶችንም በማሳለጥ የከተማዋን ገጽታ በማስዋብና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ይህንን መሰል ግንባታዎች ወጪ አድርገን ስንገነባ አገልግሎት ሰጪ አካላት በበኩላቸው ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።